Amharic Tube - All Amharic TV Channels and Shows
Welcome
Login

News


 • Ethiopian PM Meles Zenawi is on "vacation" Abroad [Ethiopian Reporter]

   ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከሐኪሞቻቸው ባገኙት ምክር መሠረት በውጭ አገር በዕረፍት ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለባቸው ከፍተኛ የሥራ ጫና ምክንያት ላጋጠማቸው ሕመም ረዘም ያለ ዕረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ይህንኑ በውጭ አገር እየፈጸሙ እንደሆነ ታውቋል፡፡

  ባለፈው ሳምንት የመንግሥት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዕረፍት ላይ እንዳሉ ገልጸው፣ ከሕመማቸውም እያገገሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዕረፍት ጊዜያቸውን በአሜሪካ እያሳለፉ ነው ቢባልም፣ ምንጮቻችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደኅነንት ሲባል ያሉበትን አገር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን የገለጹት ምንጮች፣ መቼ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ በውል እንደማይታወቅ ተናግረዋል፡፡

  የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤንነት ጉዳይ አሁንም የከተማው ዋነኛ መነጋገሪያ መሆኑን ቀጥሏል፡፡ መንግሥት ስለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መታመም ለሕዝብ ይፋ ያላደረገበት ምክንያት የኢሕአዴግ ፓርቲ ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ባለው ባህል መሆኑ በአቶ በረከት መገለጹ ይታወሳል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት ለመጀመርያ ጊዜ በ19ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕክምናቸውን እየተከታተሉና በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡ Read more »
 • የፍልፍሉና የቁልሉ ጨዋታ በጣም አስቂኝ ቃለ ምልልስ Very Funny Interview with Filfilu

  (ዘ-ሐበሻ) ቁልሉ (ወንደሰን አውራሪስ) ከፍልፍሉ (በረከት በቀለ) ጋር ብዙ ጊዜ አብሮ የሰራ ኮመዲያን ነው፡፡ ዛሬ ግን ቁልሉ ጋዜጠኛ በመሆን ፍልፍሉን ይጠይቀዋል፡፡ እነሆ ቃለ – ምልልሳቸው፡-
  ቁልሉ፡- ልጀምር?
  ፍልፍሉ፡- ፊሽካ እስኪነፋ ነው የምጠብቀው?
  ቁልሉ፡- ታዲያ ምነው ፊትህ ሾለ?
  ፍልፍሉ፡- ያንተን ፊት ስፋት አይቼ እንዳንለያይ ብዬ ነው፡፡
  ቁልሉ፡-የእኔ ፊት እኮ መሬት በሽጉጥ መሳት ነው፡፡
  ፍልፍሉ፡- የታወቀ ነው፡፡ ይልቅ ወደ ቁም ነገሩ እንግባ… እንግዲህ ብዙ ጊዜ ጋዜጠኞች አርቲስቶችን ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ገጠመኝ የሚጠይቁት መጨረሻ ላይ ነው፡፡ እኛ እስቲ ለየት እናድርገውና እዚህ ጋር ገጠመኛችንን እናውራ?
  ቁልሉ፡- በጣም ጥሩ ነው…የሆነ ጎደኛዬ ነበር፡፡ አሁን ውጪ ሃገር ሄዷል፡፡ ብዙ ጊዜ አብረን ነበር የምንሠራው፡፡ ሰዎች በመንገድ ሲያገኙን ግን ለእኔ ነው አድናቆታቸውን የሚገልፁልኝ ‹‹ማታ ቲቪ ላይ አየንህ ጥሩ ነው›› ይሉኛል፡፡ በዚህ ጊዜ አብሮኝ ስለሠራ እሱንም እንዲያደንቁት ‹‹እሱም አብሮኝ ነው የሠራው›› አልኳቸው፤ በዚህ ጊዜ ‹‹እሱን አናውቀውም አንተን ነው›› ሲሉኝ በጣም ተናደደ፡፡ ላረጋጋው ስሞክር ይባስ ተበሳጭቶ ‹‹እንዴት እኛ እንታይ… ይህን የሚያክል 21 ኢንች ፊት ይዘህ እንዴት እንታይ›› አለኝ፡፡
  ፍልፍሉ፡- ታዲያ ስክሪኑን ስትሞላበት ምን ያድርግ.. ይኸው እኔን ራሴን መንገድ ላይ እየከለልከኝ ተቸግሬ የለ…
  ቁልሉ፡- እኔ ፊት ለፊት ነው የከለለልኩት አንተስ በጎን እየሸፈንከኝ አይደል… እንደ ዶሮ፡፡… አንተ ግን ፍልፍሉ ለምን ተባልክ?
  ፍልፍሉ፡- ፍልፍሉ የተባልኩት ከብዙ ዓመታት በፊት በክበባት ውስጥ እሳተፍ በነበረ ጊዜ የሆነ ነገር እፈለፍላለሁ፡፡
  ቁልሉ፡- ነገር መፈልፈልማ አሁንም አብሮህ ነው፡፡
  ፍልፍሉ፡፡- አዎ! ሆቢዬ ነው!… እና በዚያ ሠዓት አስተያየትና ትችት ሣቀርብ ብዙዎች ያላዩትንና ያላስተዋሉትን ነገር ነው የማነሳው፡፡ በዚህ ወቅት ነው አንድ የክበባችን አባል ‹‹ይሄ ልጅ ነገር ይፈለፍላል›› ያለችኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ፍልፍሉ የተባልኩ ይኸው እስከዛሬ እየፈለፈልኩ ተቀምጫለሁ፡፡ አንተስ ቁልሉ የተባከው እንዴት ነው?
  ቁልሉ፡- መልስህ እኔኑ ትጠይቀኛለህ?… ብዙ ድራማዎችን የሠራሁት ወንደሰን አውራሪስ በሚለው ዋና ስሜ ነው፡፡ ቁልሉ ብለህ ያወጣህልኝ አንተ ነህ… ስለዚህ ለምን ቁልሉ እንዳልከኝ ራስህ ተናገረው፡፡
  ፍልፍሉ፡- እኔ ነገር ስፈለፍል አንተ ተቆልለህ ነው የምታየው፡፡ ለዚህ ነው፡፡
  ቁልሉ፡- ብዙ ሰዎች የድሮ ትዝታቸውን ሲናገሩ እንትና የሚባል ጎደኛ ነበረኝ አሁን ውጪ ሃገር ሄዷል፡፡ እንትና የሚባል ልጅ ነበር አሁን አውሮፓ ነው ያለው እያሉ ያወጋሉ፡፡ አንተ ግን ብዙ ጊዜ ስትናገር ‹‹እንትና የሚባለው ጎደኛዬ ነፍሱን ይማረውና፣›› ‹‹እከሌ የሚባል ልጅ ነፍሱን በገነት ያኑረውና›› እያልክ ስትናገር ነው የምሰማህ፡፡ አንድም ‹‹በህይወት ያለ ጎደኛዬ…›› ብለህ ስትናገር አልሠማሁም፡፡ ለምንድን ነው?
  ፍልፍሉ ፡- እኔንጃ!… ብዙዎቹ የእውነት ሞተው እንዳይመስልህ፡፡ በቁም የሞቱትንም እንደዚያ ነው የምላቸው፡፡ የዕውነት የሞቱትም ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ቢሆንም በህይወት ያሉ ከእኔ በበለጠ ደረጃ ላይ የሚገኙ በጣም የምወዳቸው ብዙ ጎደኞች አሉኝ፡፡… ይልቅ አንድ ገጠመኜን ልንገርህ?
  ቁልሉ፡- የሚያስቅ ነው ወይስ የሚያሳዝን?
  ፍልፍሉ፡- ሊያሳዝን ነው የሚችለው… አቶ ተሾመ የሚባሉ ጉረቤት ነበሩ፡፡ ቴዲ ከሚባል ልጃቸው ጋር የታሰረውን ውሻ ምንም ሳያደርገን በድንጋይ እንቀጠቅጠዋለን፡፡ ሁሌ እንዲያ ስናደርገው ቆይተን አንድ ቀን ሠንሠለቱን በጥሶ መጣ፡፡ ድንገት ስለሆነ እንዴት እንደሮጥኩ አላውቅም፡፡ ሰው ፌንጣ ሲሆን አይተህ ታወቃለህ?… ብድግ ብዬ የሆነ መስኮት ላይ ወጣሁ፡፡ ውሻው እኔን እንደማያገኝ ሲያውቅ ወደ ጎደኛዬ ዞረ፡፡ ጎደኛዬ ደግሞ በድንጋጤ ሲሮጥ ሲል ልብስ ሊታጠብበት የፈላ ውሃ ላይ በቂጡ ተቀመጠበት፡፡ እልህ ተሞልቶ ወደ ልጁ የሮጠው ውሻ የሆነውን ነገር ሲያይ ሽምቅቅ ብሎ ፊቱን አዞረና እንባውን እየዘራ ተመለሰ፡፡ ለልጁ አለቀሰለት፡፡
  ቁልሉ፡- አዝኖለት ነው?
  ፍልፍሉ፡- አዎ!… እኔ ውሻ ለሠው አዝኖ ሲያለቅስ ያየሁት ያን ዕለት መው፡፡ በኋላ ወደ ልጁ እየሮጥኩ ሄጄ ሳነሳው ስል ‹‹ተው አትንካኝ አበብዬን ጥራልኝ›› አለኝ፡፡ አበብዬ እናቱ ናቸው፡፡ እኔ ደግሞ እሳቸው እንዳይሰሙ ብዬ እንደምንም አባብዬ ሳነሳው ‹‹ሽንት ቤት ውሰደኝ›› አለኝ፡፡ ‹‹ኧረ ይሠፋብሃል›› ብዬ የነፈረውን ቂጡን በቀዝቃዛ ውሃ አበረድኩለት፡፡… ለፕሮሞሽኑም እንዲሆን እስቲ ስላወጣነው ‹‹ፍልቅልቅ›› ኮሜዲ ሲዲ እናውራ… እንዴት ነው ሠዎች ስቀውልናል? ወይስ አልቅሰውልናል?
  ቁልሉ፡- እኔ የራሳችን ስለሆነ አጋነንከው አትበለኝና ስራችን በጣም ጥሩ እንደሆነ ነው የማነው፡፡ ግን እኛ ስለራሳችን ስራ ማውራት ስለሌለብን ህዝቡ እንዲፈርድ ነው መተው ያለብን፡፡ ደግሞ ህዝቡም ጥሩ አስተያየት ስለሠጠን በበኩሌ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
  ፍልፍሉ፡- አዎ! አንዳንድ ሊስተካከሉና ሊታረሙ ይገባቸዋል ተብለው የተነገሩን ገንቢ አስተያየቶች እንዳሉ ሆነው በአጠቃላይ የተሠጠን ድጋፍና ሞራል ለቀጣይ ስራችን ትልቅ የሞራል ስንቅ ነበር፡፡
  ቁልሉ፡- ወደ ኪነጥበብ ህይወት ስትገባ መነሻ የሆነህ ምንድን ነው?
  ፍልፍሉ፡- መነሻዬ ከቤት ነው፡፡ ከቤት ተነስቼ ወጥቼ…
  ቁልሉ፡- ልጠይቅህ የፈለግኩት ለኪነጥበብ ህይወትህ አርአያ (ሮል ሞዴል) ስላደረግከው ሰው ነው፡፡ እኔ ለምሳሌ ወደ ኮሜዲ ህይወት የተሳብኩት በደረጀና ሃብቴ ነው፡፡ አንተስ?
  ፍልፍሉ፡- የእኔ መነሻዬ እማዬ ነች… አያቴ በጣም ቀልደኛ ስለሆነች የእኔ መነሻ እሷ ነች፡፡
  ቁልሉ፡- አንተ በጣም ጥሩ ጭነቅላት ነው ያለህ፡፡
  ፍልፍሉ፡- ኧረ!… የእኔ ከአንተ በልጦ??
  ቁልሉ፡- ጭንቅላትህ ስልህ ፀጉር የሚበቅልበትን ማለቴ አይደለም፡፡
  ፍልፍሉ፡- ታዲያ ጥሩ አእምሮ አለህ ነዋ የሚባው፡፡
  ቁልሉ፡- እሺ!… ጥሩ አዕምሮ አለህ፡፡ ይህን የምልህ የእውነቴን ነው፡፡ ኮሜዲ በጣም ነው የምትችለው፡፡ እንደውም እኔ በድራማ መልክ ከምታቀርበው የኮሜዲ ጨዋታ ይልቅ እንዲሁ ስንጫወትና በግል ስናወራ ነው በጣም የምታስቀኝ፡፡
  ፍልፍሉ፡- እኔ ግን አንተ ስትስቅ በጣም ነው የምናደደው፡፡
  ቁልሉ፡- ለምን?
  ፍልፍሉ፡- ባለፈው የሆነ ችግር ገጥሞኝ ደውዬ ስነግርህ የሳቅክብኝ ጊዜ እንዴት እንደተናደድኩ እኔ ነኝ የማውቀው፡፡
  ቁልሉ፡- ድራማ ላይ የማውቀውን ድምፅና አለቃቀስ ሠምቼ እንዴት መሳቅ ይነሰኝ?
  ፍልፍሉ፡- እኔን በጣም ግራ ያጋባኝ ምሬንና ቀልዴን እንዴት እንደምለየው ነው፡፡
  ቁልሉ፡- አንተ በጣም የምታሰቀኝ ከድራማ ውጪ በግል ስንጫወት ነው፡፡ ብዙ ሰዎችም ድራማ ከምትሠራው ይልቅ እንዲሁ ነፃ ሆነህ ስትጫወት ነው በጣም የምታሰቃቸው፡፡ በስራ ሙድ ውስጥ ስትሆን ግን አስቂኝ ነገርህ በግል ስንጫወት የምታሰቀንን ያክል አይደለም፡፡ ለምንድን ነው?
  ፍልፍሉ፡- ይሄ ካሜራ የሚባለው ነገር ነፃነትህን ያናጋዋል፡፡ እኔ ካሜራ ፊት ከመቆም እልም ያለ ጦርነት ውስጥ ቆመህ ጠብቀኝ ይዤ ብገባ ነው የምመርጠው … ካሜራ በጣም ነው የምፈራው፡፡
  ቁልሉ፡- ልደትህን አክብረህ ታውቃለህ?
  ፍልፍሉ፡- እቅጥረዋለሁ እንጂ አክብሬው አላውቅም፡፡
  ቁልሉ፡- ልደትህን በድግስ አክብረህ አታወቅም?
  ፍልፍሉ፡- ሻማ ተደርድሮ እፍ… እያሉ ማጥፋት ምናምን…? አድርጌው አላውቅም፡፡
  ቁልሉ፡- ለምንድን ነው?… በእናንተ ጊዜ ሻማ አልነበረም?
  ፍልፍሉ፡- በል አቁም!… ዘለህ ዕድሜ ውስጥ ልትገባ ነው፡፡… ቁልሉ ተው!… የእድሜ ነገር አይነሳ፡፡ አንተም ተቆፍረህ ስላልወጣህ እንጂ ወንዱ ሉሲ ነህ፡፡ በርግጥ እኔም ዳይኖሠር ጋልቤአለሁ፡፡
  ቁልሉ፡- እስቲ ከዚህ በፊት ስለሰራኸውና ከዚህ በኋላ ስለምትሰራው ስራ ንገረን
  ፍልፍሉ፡- እንደምታውቀው እኔ በቪሲዲ ደረጃ የመጀመሪያ ሥራዬ ከማስተር ፊልም ፕሮዳክሽን ጋ የሠራሁት ትዝታና ጨዋታ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ አንዳንድ ሥራዎችን ሠርቻለሁ፤ እስከአሁን ግን አልወጡም፡፡ ምናባት በቀጣይ ጊዜያት ሊወጡ ይችላሉ፡፡ እኔ ግን ደስተኛ አያደርጉኝም፡፡
  ቁልሉ፡- ለምን?
  ፍልፍሉ፡- ደስተኛ እሆን የነበረው እዚያ የዐዕምሮ ደረጃ ላይ እያለሁ ቢወጡ ነበር፡፡ ገና ያልበሰለና ያልዳበረ አዕምሮ እያለኝ የሠራኋቸው ናቸው፡፡ አሁን በብዙ መልኩ ተቀይሬአለሁ፡፡ ትልቅ የዐዕምሮ ብስለትና የሙያ እውቀት አግኝቻለሁ፡፡ ስለዚህ የያኔዎቹን ስራዎች አሁን ያለው አዕምሮዬ ብዙም ሊቀበለው አይችልም፡፡
  ቁልሉ፡- ሥራዎቹ ከዚህ በኋላ ቢወጡም ህዝቡ የድሮ ስራዎችህ እንደሆኑ ስለሚለይ አንተን በእነዚያ ስራዎች እንደማይመዝንህ አምናለሁ፡፡
  ፍልፍሉ፡- አዎ! እኔም ስራዎቹ አሁን ባለው የአዕምሮ ደረጃዬ የተሰሩ እንዳልሆኑ እንዲታወቅልኝ ነው የምፈልገው፡፡
  ቁልል፡- ስለቀጣዩ ጊዜስ ምን እያሰብክ ነው?
  ፍልፍሉ፡- እንግዲህ ከዚህ በኋላ እኔና አንተ በጥምረት ብዙ ስራዎችን በ‹‹ፍልቅልቅ›› እንደምንቀጥል ነው የሚሠማኝ፡፡ ‹‹ፍልቅልቅ›› አንድ ወጥቷል፡፡ በቅርቡም ፍልቅልቅ ሁለት ይወጣል፡፡ ከዚያም ፍልቅልቅ ሶስት፣አራት … እያለ ይቀጥላል፡፡ ቁጥርና እኛ እስክናልቅ ፍልቅልቅ አይቆምም፡፡
  ቁልሉ፡- ህይወት እንዴት ናት?
  ፍልፍሉ፡- እግዚአብሔር ይመስገን ጠይም ናት፡፡ አትከፋም አትለማም ተመስገን ነው፡፡… እስቲ ምን አይነት ባህሪ እንዳለኝ ንገረኝ፡፡ የዋህነቴና ደግነቴ ምን ያህል እንደሆነ ለአንባቢያን እንዲሆን አድርገህ ተናገረው
  ቁልሉ፡- አብዛኛው ሠው በቲቪ የሚያይ ስራችንን እንጂ እውነተኛ ማንነታችንን አያውቅምና ጥያቄህ ተገቢነት ያለው ነው፡፡ እንግዲህ አንተ ከሰው የመግባባት ልጅ ተሰጥኦ አለህ፡፡ ግልፅ ነህ፡፡ ነገር ግን ቸልተኝነት አለብህ፡፡ በጣም የምጠላው ባህሪህን ደግሞ ሰው ቀጥረህ ሞባይልህን የምታጠፋት ነገር ነች፡፡ አንዳንዴ ሲ.አይ.ኤ እየፈለገህ ያለ ሁሉ ይመስለኛል፡፡
  ፍልፍሉ፡- ሞባይሌን የማጠፋው ራሴን ከማጠፋ ብዬ ነው፡፡… ዋናው ምክንያቱ ይሉኝታና ሠው አለማስቀየም ነው፡፡ ከሠዎች ጋር የቁም ነገር ቀጠሮ ኖሮኝ ስገናኝ ስልኬ አርባ ሠባት ጊዜ ከየአቅጣጫው ይደወልበታል፡፡ ከነዚህ ደዋዮች ውስጥ ብዙዎች መጥተው ሊወስዱኝ የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ስለዚህ የቁም ነገር ቀጠሮዬን ለማሣካት ወይም አብሮኝ ያለውን ሠው ላለማስቀየም ስል ስልኬን እጠፋለሁ፡፡
  ቁልሉ፡- መቼስ ሞባይል የሚያገልግለው መረጃ ለመቀያየር ነው፡፡ የት ነህ? እንዴት ነህ? ልንባባልበት ዘመኑ ያበረከትልን ልዩ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ አንተ እንዳልከው ይህ ላለማስቀየም እዚያኛው ላይ ከመዝጋት ይልቅ ሲደውል ከሰው ጋር እንደሆንክና እንደማይመችህ መንገር ነው የሚሻለው፡፡
  ፍልፍሉ፡- አልለምድ ያልኩት ነገር ነው እንግዲህ ወደፊት አሻሽላለሁ፡፡
  ቁልሉ፡- ጎሽ! ሲመክሩት እሺ ብሎ የሚሠማ ልጅ ደስ ይላል፡፡ በኋላ ስንወጣ ከረሜላ እገዛልሃለው እሺ
  ፍልፍሉ፡-እሺ ደስታ ከረሜላ ነው የምፈልገው፡፡
  ቁልሉ፡- በል ደግሞ ስለ እኔ ባህሪ ንገረኝ
  ፍልፍሉ፡-ያው ታስነቅለኛለህ፡፡ አንድ ቀጠሮ ላይ አስር ደቂቃ ካረፈድኩ ለአስር ሠዓት እንዳብድ አድርገህ ታሽረኛህ፡፡ ከዚህ ውጪ ከሰው ጋር ያለህን አቀራረብና ከእኔ የበለጠ ቁም ነገረኛነትህን እወድልሃለው፡፡ አንዳንድ መ/ቤቶች አብረን ስንሄድ ከእኔ ይልቅ አንተ ነህ በትዕግስት ጉዳዩን አስረድተህ የምታሳምነው፡፡ ተነጋግረም ሣንግባባ ስንቀር እኔ ቶሎ እበሳጫለሁ፡፡ አንተ ግን በትዕግስት ለማስረዳት ትሞክራለህ፡፡ ይሄ በጣም የምወድልህ ባህሪህ ነው፡፡
  ቁልሉ፡- እስቲ ስለ ስፖርት እናውራ… ኳስ ትወዳለህ?
  ፍልፍሉ፡- ኦ! ፉትቦል… እኔ በበኩሌ ኳስና ዳንስ አይሆኑኝም፡፡
  ቁልሉ፡- ለምን?

  ፍልፍሉ፡- በህይወቴ ኳስን አንድም ቀን መትቻት አላውቅም፡፡ እሷ ነች መጥታ የምትመታኝ፡፡ ተመልካች ሆኜም ከህዝቡ ለይታ የምትመታው እኔን ነው፤ ምን እንዳደረኳት አላውቅም፡፡
  ቁልሉ፡- በረኛ ሆነህ ስለሆንከው እስቲ ንገረኝ … የሚያወቁህ ሠዎች እንኳን ኳስ የአደራ ገንዘብ መያዝ እንደማትችል ሲናገሩ ሠምቻለሁ፡፡
  ፍልፍሉ፡- አዎ!… አሞና የሚባል የሠፈራችን ቡድን አሠልጣኝ በረኛ አድርጎኝ እየተጫወትን ሳለ አንድ የተናቀናቃኝ ቡድን ተጫዋች ኳሷን አክርሮ ሲመታት እንቅ አድርጌ ቀለብኳት፡፡ እሷን እቅፍ አድርጌ እንደያዝኩ ቆሜ ወደ ሜዳው ሣይ የዕኛ ልጆች ተክዘው ቆመዋል፡፡ የተቀናቃኙ ቡድኑ ተጫዋቾች ደግሞ ይጨፍራሉ፡፡ ምን ሆነው ነው የተከዙት? ብዬ ማሰላሰል ውስጥ ገባሁ፡፡ ኳሷን እንቅ እንዳደረኩ ወደ ህዝቡ ስመለከት ከፊሉ ተክዟል ከፊሉ ይጨፍራል፡፡ በኋላ ነገሩ ግራ አጋብቶኝ ቆሜ ሳለ አሠልጣኛችን በጎሉ ጀርባ ነጥቶ ‹‹ሆድህ ቀዳዳ ነው›› አለኝ፡፡ ዞር ብዬ ሣይ ኳሷ መረቡ ውስጥ ነች፡፡ የያዝኩት ሆዴን ነው፡፡ የእውነት ሆዴ ተቀዶ ኳሷ የሾለከች መስሎኝ ሆዴን ፈትሼዋለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሠፈር ልጆች በረኛ ስደርሳቸው ያለቅሳሉ፡፡
  ቁልሉ፡- እኔ የማልረሳው ድሮ ጃንሜዳ ኳስ ስንጫወት በፕሮጀክት ታቅፈን በምንጫወት ሰዓት ዜሮ ሶስት ቀበሌ የሚባል ቀበሌ አለ ወደ ጃንሜዳ፡፡ ኳስ በጣም ጎበዞች ናቸው፡፡ ከእነርሱ ጋ ለዋንጫ ጨዋታ በደረስን ጊዜ የእኛ ደጋፊ ዘጠኝ ናቸው፤ የእነርሱ ጃሜዳ ሙሉ ነው፡፡ ሁሉም ችቦ ይዟል፡፡
  ፍልፍሉ፡- እናንተን ሊያበሯችሁ ነው?
  ቁልሉ፡- ታዲያ… እኛም ጠንካሮች ነን እነሱም አይበገሩ ፡፡ በኋላ ጨዋታው መሀል ከላይ ከጎሉ ጀርባ መጥተው ‹‹ በቃ ለኮስንህ›› ይሉኛል፡፡ ጥቂት ይቆዩና ‹‹ቂጥህ ነደደ›› ይሉኛል፡፡ በየደቂቃው እየሽማቀቅኩ ቂጤን ቼክ ሳደርግ ቆይቼ እግዜር ይስጠው ተካላካያችን የራሳችን ጎል ላይ ኳሷን ሲነክራት ጃንሜዳ እንዴት ትልቅና ተሩጦ የማያልቅ እንደሆነ ያወቅኩት ያኔ ነው፡፡
  ፍልፍሉ፡- እስቲ እኔም አንድ ልጨምር… የእኛ ጎረቤት አቶ ተስፋዬ ዘውዴ የሚባሉ አሉ፡፡ የህግ ጠበቃ ናቸው፡፡ የእሳቸው ልጆች ሁልጊዜ ከፍለፍሉ ጋር ነው የምንበላው ይላሉ፡፡ ከእሱ ጋር ካልሆነ አንበላም ስለሚሉ እኔ ጋር እንዲበሉ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ምግብ በልቶ የጨረሰ አንድ ለስላሳ ስለሚሽለም ዘለው እኔ ጋር ይመጡና ለእኔ ነው የሚሰጡኝ እኔ ደግሞ ጥርሴ እስኪግል ነው የምበላው፡፡
  ቁልሉ፡- አውቃለሁ!… ከአፍህ እንፋሎት ሲወጣ ነው የምታቆመው፡፡
  ፍልፍሉ፡- አዎ! መጥገቤን ባልንጀራዬ ነው የሚነግረኝ፡፡ ያንን ጥርግ አድርጌ ስበላላቸው‹‹ማሚ ጨረስን›› እያሉ ወደ ለስላሳው ይሮጣሉ፡፡ የሚገርመኝ ግን እስከአሁንም ያ ቤተሰብ ጉዴን አያውቀውም፡፡ ያወቀ እለት ወዮልኝ፡፡ በኋላ ላይ ትንሹ ልጅ ታሞ ሳጫውተው ቆየሁ፡፡ የዚያን ዕለት ፕሮግራም ስለነበረኝ ሱፍ ስለብስ ከውጪ የመጣ ሬሣ ነው የምመስለው፡፡ ግን ግዴታ ስለሆነብኝ ለብሻለሁ፡፡ በኋላ ከረባቴን እየጎተተ ሣሎኑን በዳዴ ያዞረኛል፡፡
  ቁልሉ፡- ውሻው ነው?
  ፍልፍሉ፡- አታዳምጥም ማለት ነው፡፡ የታመመው ልጅ አልኩህ… እያጫወትኩት ሲጎትተኝ እንድትቆጣው ብዬ እናትየውን ቀና ብዬ ሳያት ‹‹ጎበዝ ቤቢን አጫውተው›› አለችኝ፡፡ ይህ አልበቃ ብሏት ‹‹ቤቢዬ ተጫወት እንደውም ጀርባው ላይ ውጣ›› አለችው፡፡
  ቁልሉ፡- በጣም ያዘንክበት ቀን መቼ ነው
  ፍልፍሉ፡- ኧረ! እኔ መቼ ደስ ብሎኝ ያውቃል?
  ቁልሉ፡- አሁን አሁን እንኳን ደህና ነህ፡፡
  ፍልፍሉ፡- እንግዲህ እኔ በጣም አዘንኩበት የምለው ቀን ከቤት የወጣሁበትን ነው፡፡ ራሴን ችዬ ለመኖር ከቤተሰቦቼ ቤት ወጥቼ በችዬን መኖር ከጀመርኩበት ቀን በቁም የተቀበርኩበት ያክል ያዘንኩበት ነው፡፡ ራሴን ቻልኩ ብዬ ራሴን ላጠፋ የነበረበት ቀን መቼም አይረሳኝም፡፡ አንተስ?
  ቁልሉ፡- እኔ ደግሞ የኪነ ጥበብ ህይወት ውስጥ የገባሁበት ቀን ነው፡፡
  ፍልፍሉ፡- ምነው?
  ቁልሉ፡- እንዴት ምነው ትላለህ …? እስቲ ከእኛ ህይወት ውስጥ ማነው በሙያው ደስታን የተጎናፀፋት፡፡ እኛ እንሠራለን፡፡ እውቅናው አለ ተጠቃሚው ግን ሌላ ነው በዚያ ላይ ልተውህ ስትለው አይለቅም፡፡ እንደ አሚር ከያዘ ያዘ ነው፡፡ ለማንኛውም እስቲ ስለጓደኞችህ እናንሳና የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፡፡
  የምታስተወዋውቀኝ የድሮ ጓደኞችህ ወይ እንዳንተ የፊት ጥርስ የላቸውም፡፡ ወይ ግንባራቸው ተበይዷል፡፡ ወይ አፍንጫው ተተርትሯል መንታዎችህ ነው የሚመስሉት… ምክንያቱ ምንድን ነው?
  ፍልፍሉ፡-አስገባህልኝ! ወይኔ!… ሁላችንም እንደፈጣን ተፋፍቀን አለቅን፡፡
  ቁልሉ፡- አንተ ብዙ ሰዎችን ታስቃለህ አንተን የሚያስቅህ ማነው?
  ፍልፍሉ፡-እኔንጃ!… ብዙ ኮሜዲያን አሉ፡፡ እከሌን ብሎ ለይቶ መናገር ይከብደኛል፡፡
  ቁልሉ፡- በሀገራችን ኮሜዲና ኮሜዲያን አለ?
  ፍልፍሉ፡- በትክክል አለ
  ቁልሉ፡- ቁጥራችን በቂ ነው?
  ፍልፍሉ፡- እንዴት ተደርጎ!… ለሰባ ምናምን ሚሊዮን ህዝብ በጣት የሚቆጠሩ ኮሜዲያን እንዴት በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ የሀገራችን ህዝብ ራሱ በጣም ኮሜዲ ነው፡፡
  ቁልሉ፡- ኑሮው እኮ ነው ኮሜዲ ያደረገው፡፡ ኑሮ ከአቅም በላይ ሲሆንበት ህይወት በቀልድ መግፋት ጀምሯል፡፡ ታክሲ ውስጥና ካፌዎች አካባቢ የምሰማቸው ቀልዶች እኛ ኮሜዲያኑ ከምናቀርባቸው የላቁ ናቸው፡፡ በተለይ ወጣቱ ሁሉም ቀልደኛ ሆኗል፡፡
  ፍልፍሉ፡- ህዝቡ የሚቀልደውን ያህል እንዳንቀልድ እኮ ገደቡም ተፅእኖ አለው፡፡ እኛ እንዳንቀልድ ገደብ የተጣሉብን ጉዳዮች ብዙ ናቸው፡፡ በመሠረቱ የአንድ ኮሜዲ ተልዕኮ ሣቅ መፍጠር እስከሆነ ድረስ ገደብ ሊበጅለት አይገባም ነበር፡፡
  ቁልሉ፡- ልክ ነህ!… የኮሜዲ ተልዕኮ በማኛውም ነገር ላይ መቀለድና መሣቅ እስከ አሁን ድረስ ገደብ ሊደረግ አይገባውም ነበር፡፡ የእኛ የኮሜዲያን አላማችን ህበረተሰብን ማሣቅ ነው፡፡ በማንኛውም ርእሰ ጉዳይ ላይ ሣቅ የሚፈጥር ነገር መናገር ስለማንችል ህዝቡ በቀልድ በልጦን ሄዷል፡፡ በየቤቱና በየሠፈሩ የሚሳቅባቸው ጉዳዮች በእኛ አፍ እንዳይነገሩ ገደብ መጣሉ አግባብ አይመስለኝም ፡፡ ፈጠራን ያቀጭጫል፡፡
  ፍልፍሉ፡-ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ ጉዳዮች እየተነሱ ሣቅ እንዲፈጠርባቸው ካልተቻለ የኮሜዲ ሙያ በዚህች አገር የት ቦታ እንደሚደርስ እድሜ ከሠጠን አብረን እናየዋለን፡፡ በመሠረቱ እንዳንቀልድባቸው የተከለከሉት ሁሉ አዲስ ነገሮች አይደለም፡፡ ህብረተሰቡ የሚያውቃቸው ናቸው፡፡ እኛ አሳምረን እናቀርባቸው እንደሆነ እንጂ ሁሉም የሚታወቁና ውስጥ ውስጡን እየተሳቀባቸው ያሉ ናቸው፡፡
  ቁልሉ፡- መፍትሔው ምን ይመስልሃል?
  ፍልፍሉ፡- እኔ መድሃአለም ይፍታው ነው የምለው፡፡
  ቁልሉ፡- አመሰግናለሁ፡፡ S

  Read more »
 • Ethiopia’s PM Zenawi ‘critically ill’

  Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi was reported to be in a ‘critical’ state this morning in a Brussels clinic, the AFP quoted yet to be identified diplomats as revealing.

  Rumours about Zenawi’s death spread in Addis Ababa in the last few days when he missed the African Union’s two-day summit.

  Meles’s wife, herself a lawmaker, declined to talk to reporters about her husband, while government officials were not available to comment.

  The Ethiopian embassy in Brussels denied reports he was being treated at a hospital there as “false and wrong”, calling it a rumour created by “an interest group which has preoccupied itself in disseminating such untrue stories”.

  It is believed to be the first time Meles has missed the AU summit in the Ethiopian capital. Meles, 57, has been at the helm of the Horn of Africa nation since 1991.

  Dozens of African heads of state visited Ethiopia for the summit, including newly elected Egyptian President Mohamed Morsi, the first to do so since an assassination attempt in Ethiopia on former president Hosni Mubarak in 1995.

  Benin’s president and current AU chairman Thomas Boni Yayi said at the opening of the summit Saturday that the “unusual absence… cannot go unnoticed, because we know that Mr Meles is full of dynamism and leadership in our meetings”.

  Ethiopia’s Deputy Prime Minister and Foreign Affairs minister Hailemariam Desalegn sat in for Meles at the AU opening session.

  One of last times Meles was seen in public was at the G20 meeting in Mexico on June 19.

  Just today, the United Nations human rights commissioner, Navi Pillay drew attention to the ‘climate of intimidation’, gaining ascendancy in the country.

  Journalists and human rights campaigners are the target of “overly broad” anti-terrorism laws in Ethiopia where there is a “climate of intimidation”, the top UN expert said.

  “The once vibrant civil society in Ethiopia has been whittled away as the space for them to operate freely has rapidly shrunk since the 2009 Charities and Societies Proclamation was passed into law,” Pillay said in a statement from the Office of the High Commissioner for Human Rights (OHCHR) in Geneva.

  “The dramatic reduction in the number of organisations working on human rights issues, particularly on civil and political rights, is deeply disturbing.”

  Some 20 Ethiopians, including journalist-blogger Eskinder Nga, were jailed on July 13 for up to 18 years after being accused of promoting anti-government protest in Ethiopia, including by using examples of the Arab Spring uprisings in the media.

  Pillay said the “overly broad definitions in the July 2009 anti-terrorism law of Ethiopia result in criminalising the exercise of fundamental human rights.”

  “Taken together, such laws have created a climate of intimidation,” she added.


  Read more »
 • በአወሊያ የእስልምና ዕምነት ተከታዮችና ፖሊስ ተጋጩ

  በግጭቱ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ እየተገለጸ ነው
  -    በርካቶች በግጭቱ ምክንያት መታሰራቸው ተጠቁሟል
  -    መንግሥት ከሕገወጥ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል
   ላለፉት በርካታ ወራት ‹‹ሰደቃና የአንድነት ፕሮግራም›› በሚል በየመስጂዱ ያደርጉት የነበረውን ፕሮግራም፣ በዛሬው ዕለት ተሰባስበው በአወሊያ ኮሌጅ ለማድረግ በመንቃሳቀስ ላይ የነበሩ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ባለፈው ዓርብ ምሽት ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውን በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ በበኩሉ ሕገወጥ ስብሰባ ለማድረግና የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባን ለማወክ ሕገወጥ እንቅስቃሴ እያደረጉ ናቸው ያላቸውን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል፡፡

  በየሳምንቱ እየተገናኙ ‹‹ለሃይማኖቱ አመራር ማን ቢሆን ይሻላል?›› በማለትና በሌሎችም ሃይማኖታዊ ጉዳዮች በአገር አቀፍ ባሉ 13,900 መስጂዶች የሚገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ሲመካከሩ መክረማቸውን የሚገልጹት የእምነቱ ተከታዮች፣ ዛሬ በአወሊያ ትምህርት ቤት ለመገናኘትና ለመመካከር በየክልሉ ከሚገኙት መስጂዶች አንድ አንድ ተወካዮችን መጋበዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ለተሰብሳቢዎቹና ለሚመጡት እንግዶች ያረዱዋቸውን አሥር በሬዎች ለመሥራት እየተንቀሳቀሱ ሳለ፣ ዓርብ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን ሌላ ችግር መከሰቱን አማኞቹ ገልጸዋል፡፡

  ዓርብ ከምሽቱ 12 ሰዓት ሲሆን ቀድሞ የአወሊያ ኮሌጅ ኃላፊ የነበሩ ግለሰብ ከፖሊስ ጋር በመሆን ወደ ግቢው ገብተው፣ ለዝግጅቱ የቀረበውን ዕርድና ቁሳቁስ ይዘው መሄድ እንደሚችሉ ሲነግሯቸው፣ ፖሊሶቹ ዕርዱንና ሌሎቹን ቁሳቁስ ጭምር በመኪና ሲጭኑ፣ ድንኳን ለመጣል በግቢው ውስጥ ከነበሩትና ከሌሎቹ የዝግጅቱ ታዳሚዎች ጋር ግብግብ ቢፈጠርም፣ የከፋ ችግር ሳይደርስ ይዘው መሄዳቸውን በቦታው የነበሩ የዓይን አማኞች ጠቁመዋል፡፡

  እንደ ዓይን እማኞቹ ገለጻ፣ ከምሽቱ በ12 ሰዓት የተጀመረውንና ፖሊሶች ያደረጉትን ሁሉ በስልክ የእምነቱ ተከታዮች እንዲያውቁት ተደርጐ ስለነበር፣ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ፌዴራል ፖሊስ ተመልሶ በመምጣት፣ የግቢውን መብራት በማጥፋትና ወደ ግቢው ዘልቆ በመግባት አስለቃሽ ጭስ በመርጨት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውል፣ ጥቂቶች ማምለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

  ያመለጡት ወደ ውጭ ሲወጡ፣ ከዊንጌት ጀምሮ ወደ አስኮም ሆነ ከአስኮ ወደ ፒያሳ መተላለፊያ መንገዶች መዘጋታቸውንና ከፍተኛ የሆነ ተኩስ እንደነበር የገለጹት አማኞቹ፣ ትክክለኛ ቁጥሩን ማረጋገጥ ባይቻልም ሰዎች ሕይወታቸው ሳያልፍ እንደማይቀር በሙሉ እምነት ይናገራሉ፡፡

  በአወሊያ ኮሌጅ የፖሊስንና በሥፍራው የተገኙትን ሰዎች ግጭት የሰሙ በሌሎች መስጂዶች የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች፣ በየትኛው መስጂድ እንደሆነ ባይናገሩም፣ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ‹‹አዛን›› በመደረጉ፣ ተሰባስበው ወደ አወሊያ ኮሌጅ በመጓዝ ላይ እያሉ፣ ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ መድኃኒዓለም ትምህርት ቤት አካባቢ ሲደርሱ ፖሊስ እንዲበታተኑ ማድረጉን አማኞቹ ገልጸዋል፡፡

  አወሊያ ኮሌጅ አካባቢ ድብደባ ደርሶባቸው የተጐዱና በጥይትም ሳይመቱ እንዳልቀሩ የሚነገርላቸው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች፣ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ራስ ደስታ ሆስፒታልና ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ለሕክምና መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

  በትናንትናው ዕለት በርካታ ሙስሊሞች መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስጂድ ውስጥ መሰባሰባቸውን የሚናገሩት የእምነቱ ተከታዮች፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ሐምሌ 4 ቀን 2004 ዓ.ም. ዝናብ ሳያግዳቸው ለበርካታ ሰዓታት በዚሁ መስጂድ የተሰባሰቡ የእምነቱ ተከታዮች፣ ‹‹አንፈራም፣ በሃይማኖት አንደራደርምና አላውሃ አክበር›› በማለት ከፍተኛ ድምፅ ሲየሰሙ መዋላቸውን አስረድተዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት የተሰባሰቡት የዕምነቱ ተከታዮች ሲመካከሩና ፀሎት ሲያደርሱ ከመታየታቸው ውጭ ሌላ ነገር አለመታየቱን ገልጸዋል፡፡

  የፌዴራል ፖሊስ ዓርብ ምሽት ላይ ባስተላለፈው መግለጫ፣ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ በሚካሄድበት በዚህ ወቅት በድብቅ በመሰባሰብ፣ ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ወገኖች መኖራቸውን እንደደረሰበት ገልጿል፡፡ በመሆኑም ከተለያዩ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ በመግባት በሕገወጥ ድርጊት ላይ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ የሚገኙትን ነዋሪዎች ማጋለጥና አሳልፎ መስጠት እንዳለባቸውም አስታውቋል፡፡ ሃይማኖቱን ሽፋን በማድረግ ሕገወጥ ስብሰባ ለማድረግ በየመስጂዶች እየገቡ፣ እየበጠበጡና ኢማሞችንና አባቶችን በመደብደብ ላይ መሆናቸውን የገለጸው ፖሊስ፣ ኅብረተሰቡም ሕገወጦችን ባለመተባበር ሕገወጥ ጥሪውን የሚያስተላልፉትን አሳልፎ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

  አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የእምነቱ ተከታይ በእስልምና እምነት ተከታዮቹ አማካይነት ተፈጥረዋል ስለተባለው ችግር ሲገልጹ፣ አለመግባባቱ ከተጀመረ ስድስት ወራት አልፎታል፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤት ምርጫ ያደርጋል ከተባለ በኋላ ምክር ቤቱ ኃላፊነቱን ለመጅሊሱ ማስተላለፉን ይናገራል፡፡ በዚህ ጊዜ የዕምነቱ ተከታዮች፣ ‹‹የሃይማኖት መሪዎቹ ምርጫ ገለልተኛ ሊሆን ይገባል›› ብለው፣ የመጅሊሱ መሪዎች የተመረጡበት የአምስት ዓመት ጊዜ ስላለፈና የዕምነቱ ተከታዮችም በእነሱ እምነት ስለሌላቸው ሌላ ገለልተኛ አካል እንዲመረጥና ምርጫው እንዲደረግ መጠየቃቸውን አስታውሰዋል፡፡ 

  መጅሊሱ ግን በጥር ወር የመተዳደሪያ ደንቡን በማሻሻል፣ የሚመረጠው የሃይማኖት መሪ ለአሥር ዓመታት እንዲቆይ ማድረጉንና ምርጫውም ከነሐሴ 21 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 5 ቀን 2005 ዓ.ም. በየቀበሌው እንደሚካሄድ መግለጹን አማኞች ይቃወማሉ ብለዋል፡፡ 

  በዚህም ምክንያት ‹‹የሰደቃና የአንድነት ፕሮግራም›› በማለት በአገር አቀፍ በሚገኙ 13,900 መስጂዶች ስለሚመረጠው የሃይማኖቱ መሪ መመካከር መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ ምርጫው ሊደረግ የሚገባው በየመስጂዱ መሆን እንዳለበት፣ በየቀበሌው የሚደረገው ምርጫ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ፣ የዕምነቱ ተከታይ መሆን አለመሆኑን መለየት እንደሚያስቸግር እኚሁ አማኝ ተናግረዋል፡፡

  በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ሴቶች የወር አበባ ላይ ሲሆኑ መምረጥ ስለማይችሉና መምረጥ እንዲችሉ ምርጫው በየቀበሌው ይሁን መባሉንም የሚቃወሙት አማኞቹ፣ በሃዲስ ቁራን ነብዩ መሐመድ የተናገሩትን ቃል የሚያፈርስ በመሆኑ እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡

  ለወራት ሲካሄድ የነበረው የሰደቃና የአንድነት ፕሮግራምን ለማጠቃለልና ለመመካከር ከአሥር በላይ በሬዎችን በማረድ የክልል መስጂዶች ተወካዮችን በመጥራት ዛሬ በአወሊያ ኮሌጅ ሊያደርጉት የነበረው ዝግጅት መደናቀፉንም ገልጸዋል፡፡

  ፖሊስ ሕገወጥ ነው ባለው ስብሰባና ዝግጅት ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን፣ የፌዴራል ፖሊስንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም፡፡    Read more »
 • በጥያቄ የታጀበው የዓረብ አገር ጉዞ

  ወደ ክሊኒኩ የሚወስደው አቋራጭ ግራና ቀኝ ጥግ ጥግ ይዘው በተቀመጡ፣ እንዲሁም በሚወጡ በሚወርዱ ሴቶች ተጨናንቋል፡፡ ጥቂት ወንዶችም አሉ፡፡

  አቋራጭ መንገዱን ያጨናነቁት ወደ ዓረብ አገሮች ለመሔድ በክሊኒኩ ምርመራ ለማድረግ የተገኙ በርካታ ሴቶችና አብረዋቸው ወደ ክሊኒኩ የሔዱ ጥቂት ዘመዶችና ጓደኞቻቸው ናቸው፡፡ አቋራጭ መንገዷን ገና ገባ እንዳሉ የሚታየው ትርምስ ክሊኒኩ ውጭ ዙሪያ ገባውን ማስተዋል ይከብዳል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በክሊኒኩ ደጃፍ ላይ ዓይንን የሚይዝ ትእይንት በርካታ መሆን ነው፡፡ የተመርማሪዎቹ ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ መሆን፣ የሚናገሩት ቋንቋ መለያየት፣ የብዙዎቹ ግራ የተጋቡ መሆንና ሌሎችም ነገሮች በርካታ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ እንዲገረሙም ግድ ይላል፡፡

  መጀመርያ ላይ በሚገኘው የክሊኒኩ በር ወደ ውስጥ ዘለቅን፡፡ በሩ ላይ መሬት እፍ ብለው የተቀመጡ፣ የቆሙም ሴት ተመርማሪዎች ስለነበሩ በሩን አልፎ መግባት ቀላል አልነበረም፡፡ ሴቶቹ ቀላል እንቅስቃሴ እንኳ ማድረግ በማይችሉበት ሁኔታ በጣም ተጠጋግተው ተቀምጠዋል፡፡ ብዙዎቹ ወጣቶች ቢሆኑም ሠላሳዎቹ አጋማሽ ላይ የሚገኙ የሚመስሉም ነበሩ፡፡ ውስጥም እዚህም እዚያም ጥግ ጥግ ይዘው የቆሙ አሉ፡፡ አቀማመጣቸው ተራ የሚጠብቁ ስለመሆኑ የሚናገረው ነገር ቢኖርም መሐል መሐል ላይ ወለል ላይ የተቀመጡና የቆሙ ሴቶች መኖራቸው የቁጥራቸው መብዛት በተወሰነ መልኩ የሰልፍ ትርምስ መፍጠሩን ይመሰክራል፡፡ ለመቀመጥም ሆነ ለመቆም ምንም ዓይነት ቦታ ማግኘት ባለመቻላችን ወደ ሌላው የክሊኒኩ በር አመራን፡፡

  ከመጀመርያው ጋር ሲነፃፀር በዚህ በኩል የሴቶቹ ቁጥር ቀለል ይላል፡፡ እዚህ መቀመጫ ማግኘት ቻልን፡፡ እነዚህኞቹ ሴቶች ውጤታቸውን የሚቀበሉ፣ እነዚያ ደግሞ ገና ለመመርመር የሚጠብቁ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ለሰዓታት አንድ ላይ ጎን ለጎን ቢቀመጡም ምንም ዓይነት የቃላት ልውውጥ ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ ይልቁንም በራሳቸው ሐሳብ የተዋጡና የተጨነቁ ይመስላሉ፡፡ ጭንቀታቸው “ውጤቴ ምን ይሆናል” የሚል ለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለውም፡፡

  ሦስት አራት የሚሆኑ ሠራተኞች ወዲህ ወዲያ ይላሉ፡፡ የውጤት ወረቀትንና ፓስፖርቶች የያዙ በርካታ ነጫጭ ፖስታዎችን አንዷ እያመጣች ለሌላው ሠራተኛ ሰጥታ ትመለሳለች፡፡ ሌላዋ ደግሞ ተመሳሳይ ፖስታዎችን ይዛ በመምጣት እዚያው ፈቀቅ ብላ ስም መጥራት ትጀምራለች፡፡ ስም መጠራት ሲጀምር የሴቶቹ ጭንቀት ይበልጥ እየጨመረ እንደሚሔድ በግልፅ ይታያል፡፡ ባለሙያው ስማቸውን ሲጠራ በደስታ ተንደርድረው በመሔድ እጅ የሚነሱ፤ አመስግነው የውጤታቸውን ፖስታ የሚቀበሉ አሉ፡፡ የስማቸው መጠራት በፈጠረባቸው ስሜት “ወዬ” ብለው ውጤታቸውን ሲቀበሉ ያየናቸውም አሉ፡፡

  ከመጡ ውጤቶች መሐል የእነሱ እንደሌለበት ሲያውቁ ፊታቸው መቅላት የጀመረና የተርበተበቱ ወጣት ሴቶችም አጋጥመውናል፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹ በተለይም ከእነሱ ኋላ የነበሩ ውጤታቸውን ማግኘታቸውን ያወቁ ሴቶች ሠራተኞቹን “የእኔስ ውጤት? ከኋላዬ የነበሩ ውጤታቸውን አውቀዋል?” በማለት ደጋግመው ይጠይቃሉ፡፡ አንዳንዶቹ አንዱ ሠራተኛ የሰጣቸው ምላሽ በቂ ሳይመስላቸው ሌላኛዋን ሠራተኛ ደግመው ይጠይቃሉ፡፡ ምላሹ ቁጣና ማመናጨቅ ነው፡፡

  ምናልባትም ረዘም ላለ ሰዓት መሥራት፣ በርካታ ቁጥር ያለውን ተገልጋይ ማስተናገድ የሚፈጥረው ጫና ቢኖርም የክሊኒኩ ሠራተኞች 550 ብር ከፍለው ምርመራ በማድረግ ወደ ተለያዩ ዓረብ አገሮች የሚሔዱ ሴቶችን ማመናጨቅና መቆጣታቸው አግባብ አይደለም፡፡ ወደ ክሊኒኩ የሔዱት እንደ ማንኛውም ተገልጋይ ገንዘባቸውን ከፍለው በመሆኑ ለተገልጋይ የሚደረገውን መስተንግዶም ሆነ አገልግሎት ማግኘት ይገባቸዋልና፡፡ አገራቸው ላይ ገንዘባቸውን ከፍለው ለሚያገኙት አገልግሎት በወገናቸው በዚህ መልኩ የሚስተናገዱ ከሆነ ገንዘብ ከፍለው በሚያሠሯቸው ዓረቦች የሚደርስባቸውን ግፍ እንዴት ለመኮነን እንደፍራለን?

  የመጣችው ከትግራይ፤ የምትሔደውም ወደ አማን መሆኑን የነገረችን ወጣት ስሟ እንዲገለፅ አልፈለገችም፡፡ ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ ከክሊኒኩ መድረሷን ከኩላሊት ችግር ውጭ ምንም ዓይነት የጤና ችግር ይኖርብኛል ብላ እንደማትገምት ስትገልፅልን ትንሽ ገለል ብለው አንድ የተዘጋ ቢሮ በር ላይ ወደ ቆሙና ተቀመጡ ሴቶች አመልክተን ስለነሱ ጠየቅናት፣ “እነሱ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሚያናግራቸውን ሐኪም እየጠበቁ ነው” ብላ ትንሽ ሐሳብ የገባት መሰለች፡፡

  ጠዋት ላይ ምርመራ ካደረገች በኋላ መፀዳጃ ቤት መጠቀም ባለመቻሏ ሽንቷ በጣም እንደያዛት ነገረችን፡፡ ከጐኗ የነበረች ሌላ ልጅም እሷም ሽንቷ ይዟት እየተሰቃየች መሆኑን ስትገልጽልን ሠራተኞቹን ጠይቀው እንዲጠቀሙ ብንነግራቸውም ያልናቸውን ለማድረግ አልደፈሩም፡፡ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሠራተኞቹ እንደሚቆጧቸው ሲነግሩን መፀዳጃ ቤት መጠቀም መብታቸው መሆኑን እንዳላወቁ አልያም ሠራተኞቹ በሚያሳዩአቸው ያልተገቡ ነገሮች እዚያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እስካሉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ፍርሀት እንዳደረባቸው ገመትን፡፡

  በክሊኒኩ በነበረን አጭር ቆይታ “የኔስ ውጤት እያለች?” በተደጋጋሚ ትጠይቅ የነበረች ሴት ተመርማሪ በመጨረሻ “እንዲያውም ያንቺ ውጤት ዛሬ አይደርስም ሒጂ” ስትባል ሌላ ተመርማሪ ደግሞ ፓስፖርቷን ለማን እንደሰጠች ስትጠየቅና መልሷ ሁለት ሠራተኞችን ሲያነጋግር አይተናል፡፡

  ወደ ተለያዩ ዓረብ አገሮች የሚሔዱ በርካታ ሴቶች እንደዚያ በተጨናነቀ ሁኔታ በአንድ ክሊኒክ ምርመራ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተለያዩ ጥያቄዎች ሊነሡ ይችላሉ? የመጀመርያ ጥያቄ የሚሆነው መጨናነቁ ለምን ተፈጠረ ሲሆን በእንደዚህ ያለ የጭንቅንቅና የትርምስ አሠራር ውጤቶች ምን ያህል አስተማማኝ ይሆናሉ? ተገልጋዮቹስ እንዴት ተገቢውን መስተንግዶ ያገኛሉና ሌሎችም ተያያዥ ጥያቄዎች ይከተላሉ::

  ወደ ተለያዩ ዓረብ አገሮች በቤት ሠራተኝነት ለመሔድ ሴቶች ምርመራ የሚያደርጉባቸው ክሊኒኮች ወይም ሆስፒታሎች ውስን ናቸው፡፡ ወደ እነዚህ የጤና ተቋማት ሴት ተመርማሪዎችን የሚያከፋፍለውና ቢሮው ካዛንችስ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አቅራቢያ የሆነው ጋምካ (Gulf Countries Council Approved Medical Center Association) ነው፡፡ በዚሁ ተቋም ሥር አገልግሎት በሚሰጥ ሌላ ሆስፒታልም ተገኝተን ነበር፡፡

  እዚህ ደግሞ ተመርማሪን ለመርዳት አብሮ የሔደ ዘመድ ወይም ጓደኛ ውስጥ እንዲገባ አይፈቀድም፡፡ ይህ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊፈጠር የሚችል መጨናነቅን ለማስቀረት ታስቦ የተደረገ ቢሆንም፣ ወደ ዓረብ አገሮቹ እየሔዱ ያሉት ሴቶች በብዛት ከተለያዩ ገጠራማ የአገሪቷ ክፍሎች የሚመጡ፣ በተለያዩ ነገሮች ግራ የሚጋቡ መሆናቸው ዕርምጃ ብዙም የሚያስኬድ አይመስልም፡፡ ከሆስፒታሉ ጎን ከሚገኘው ካፍቴሪያ ተጠቅመን ወደ መጸዳጃ ቤት አመራን፡፡ በዚህ ወደ ቅጥር ግቢው መግባት ቻልን፡፡ ቆይታችን በጣም አጭር የነበረ ቢሆንም፣ በዚያች ደቂቃ ውስጥ የምትፈልገው ቢሮ ፊት ለፊት ቆማ ቢሮ ቁጥሩ የት እንደሆነ የጠየቀች ተመርማሪ አጋጥማናለች፡፡

  እዚህኛው ሆስፒታል ያስተዋልነው ለየት ያለ የሚመስል ነገር ደግሞ ከሆስፒታሉ እየወጡ ፊት ለፊት ከሚገኝ ግቢ (ምናልባትም መኖርያ ቤት) እየገቡ ፎቶግራፍ የሚነሱ ሴቶች መኖራቸው ነው፡፡ ሴቶቹ ለምርመራ ከየተመደቡበት የጤና ተቋም እስኪደርሱ ለምርመራ ውጤት ፎቶግራፍ እንደሚያስፈልግ መረጃ አለማግኘታቸው ይገርማል፡፡ ወደ እዚህ ጤና ተቋም ሒዱ ሲባል ይህን ነገር ይዛችሁ ሒዱ አይባልም፡፡ ወደ ጤና ተቋማቱ ሲሔዱ ፎቶግራፍ ይዘው እንዲሔዱ መግለጽ ወይስ ሾልከው ገብተው ፎቶ የሚነሡበት የተሸፋፈነ ሁኔታ ማመቻቸት ይቀላል?፡፡ በጤና ተቋሙ ቶሎ ለመስተናገድ ወረፋ የገዙ በሌሊትም ወደ ተቋሙ ያመሩም አጋጥመውናል፡፡

  ያገኘናት ውስጥ የገቡ የጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸውን መውጣት ከሆስፒታሉ ውጭ ግንብ ተደግፈው ከሚጠባበቁ ወጣቶች፣ እናትና አባቶች መካከል ነው፡፡ የምትጠብቀው ታላቅ እህቷን ነበር፡፡ ሰፈራቸው ፓስተር አካባቢ ነው፡፡ የጋምካን ዘጠና አንደኛ ወረፋ በ30 ብር መግዛታቸውን ለመመርመርም ተመሳሳይ ገንዘብ ሰጥተው ትንሽ ቀደም ማለታቸውን ነገረችን፡፡ ስናናግራት አምስት ሰዓት ተኩል ገደማ የነበረ ቢሆንም እህቷ እስከዚያ ሰዓት ድረስ ለመመርመር ተራ በመጠበቅ ላይ ነበረች፡፡

  ለጉዟቸው ከሚያደርጉት የሕክምና ምርመራ በተለይም በሕክምና ተቋማቱ ቅጥር ውስጥ ሴቶች የሚያጋጥማቸውን ችግር በማስመልከት ሴቶቹን ለምርመራ የሚያሰማራው ጋምካ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ ግዛውን አነጋግረናቸዋል፡፡

  ጋምካ የባሕረ ሰላጤው አገሮች የመረጧቸው የጤና ተቋማት ስብስብ ሲሆን የጤና ተቋማቱ ሦስትና ከዚያ በላይ ሲሆኑ በየአገሮቹ የየራሳቸውን ስብስብ ይፈጥራሉ፡፡ በሕንድ፣ ፓኪስታን ኔፓል ሌሎችም አገሮች በዚህ መልኩ የተፈጠሩ ጋምካዎች አሉ፡፡ የኢትዮጵያውም 2001 ዓ.ም. ላይ በአርሾ፣ ቢታንያ፣ ሃሌሉያ፣ ኬቲ ቅዱስ ገብርኤል፣ ሳንቴ፣ ሁልሸትና (ከሁለት ዓመት በፊት በራሱ ፍላጐት ከስብስቡ የወጣ) ዘንባባ ስብስብ ተቋቋመ፡፡

  የባህረ ሰላጤው አገሮች የጤና ሚኒስቴር ካውንስል እነዚህን የጤና ተቋማት የመረጠው እ.ኤ.አ. 2007 ላይ በአዲስ ዘመንና ዘ ኢትዮፒያን ሔራልድ ላይ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት መሆኑን ዶክተር ቴዎድሮስ ገልጸውልናል፡፡ የጤና ተቋማቱ በጋምካ ሥር ሆነው ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች አንዱ ወደ ዓረብ አገሮች የሚሔዱ ተጓዦችን ምርመራ ማድረግና የውጤት ማረጋገጫ መስጠት ነው፡፡ ይህን አገልግሎት ለመስጠት (ተመርማሪዎችን እኩል ለመከፋፈል) ተስማምተዋል፡፡ ፒያሳ የምትኖር ወደ ዓረብ አገር ተጓዥ አርሾ መመርመር ሲቀላት ሳሪስ ወደሚገኘው ዘንባባ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ሳሪስ የምትኖረው ደግሞ ጨው በረንዳ አካባቢ ወደሚገኘው ዛክ የምትላከው ተገልጋዮችን ለተመረጡት የሕክምና ተቋማት እኩል በማከፋፈል አግባብ መሆኑን ዶክተር ቴዎድሮስ ይናገራሉ፡፡ ይህን የተገልጋዮችን ፍላጎት ያላገናዘበ አሠራር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መሆኑን ስንነግራቸው ተረድተዋል፡፡ ገንዘባቸውን ከፍለው ምርመራውን የሚያደርጉ ሴቶች ፍላጎት እንደ ተገልጋይ መጠበቅ አለመቻሉ የሚደርስባቸው መንገላታትስ? ማንም ሊያነሣ የሚችለው ጥያቄ ነው፡፡

  በአሁኑ ወቅት በጋምካ ሥር ያሉት ስምንት የጤና ተቋማት ናቸው፡፡ ዘክና ሳይመን ስብስቡን በያዝነው የፈረንጆች ዓመት የተቀላቀሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን ኬቲ ቅዱስ ገብርኤል፣ ሃሌሉያና ሳንቴ ለጊዜው እገዳ ላይ በመሆናቸው አሁን አገልግሎቱን እየሰጡ ያሉት አምስት ብቻ መሆናቸውን ዶክተር ቴዎድሮስ ገልጸውልናል፡፡

  “እስከ አሁን ሁለት ጊዜ የታገዱ ሁሉ አሉ፡፡ ሦስተኛ እገዳ ግን የለም፡፡ ከስብስቡ መውጣት እንጂ” የሚሉት ዶክተር ቴዎድሮስ፣ መቀመጫውን ሳውዲ ሪያድ ያደረገው የባሕረ ሰላጤው አገሮች የጤና ሚኒስቴር ካውንስሉ በተለያዩ አገሮች በሚገኙ 38 በሚሆኑ ጋምካዎች ሥር የሚንቀሳቀሱ የጤና ተቋማትን በየጊዜው እንደሚቆጣጠር ይናገራሉ፡፡

  ምናልባትም የተገልጋዮች ቁጥር ከፍተኛ መሆን ለሴት ተመርማሪዎቹ በጤና ተቋማቱ ውስጥ መንገላታትና ያልተገባ መስተንግዶ ምክንያት ከሆነ በማለት ባቀረብነው ጥያቄ፤ ከቀናት በፊት አራቱ አገልግሎቱን የሚሰጡ ድርጅቶች ዝግ ሆነው ዘንባባ ብቻውን ይሠራ በነበረበት ወቅት በተፈጠረ መደራረብ እንጂ በአሁኑ ወቅት አራቱ ወደ ሥራ ከገቡ በኋላ መጨናነቅ እንደሌለ በመጥቀስ ዶክተር ቴዎድሮስ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ እኛ ግን ከአራቱ ወደ ሁለቱ በመሔድ መጨናነቅ እንደነበር አይተናል፡፡

  እሳቸው እንደሚሉት፣ ተቋማቱ በአሁኑ ወቅት በቀን በአማካይ ሦስት መቶ ለሚሆኑ ወደ ዓረብ አገር ለሚሔዱ ሴቶች ምርመራ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ቁጥር በተወሰነ መልኩ ባለፉት ቀናት በአራቱ ተቋማት መዘጋት የተፈጠረ ነው፡፡

  ሌሊት ወረፋ በሚጠበቅበት፣ ትርምስ በበዛበት ሁኔታ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ምን ያህል አስተማማኝ ይሆናል? ለሚለው ጥያቄ ተቋማቱ በቀን ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ ሲሆን ተገልጋዮችን በሚቀጥለው ቀን እንደሚቀጥሩ፣ ሌሊት ወረፋ የመጠበቅ ሁኔታ እንዳይኖር እያደረጉ መሆናቸውን በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል፡፡ የውጤት አስተማማኝነትን በሚመለከትም “የጤና ተቋማቱ ዘመናዊ መሣሪያዎች አሏቸው፡፡ በሙሉ አቅማቸው ከሠሩ በቀን እስከ 800 ሰው ሊያስተናግዱ ይችላሉ፡፡ የምርመራ ውጤት ሪፖርቱን የሚሠራው ማሽን ነው፡፡ ምናልባት ግን ውጤት ሲሰጥ የሚታየው ሁኔታ ትርምስ ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ “ዛሬ ላይ ዘለን አልመጣንም አሥርም ሀያም ሰው የሠራንበት ጊዜያት ነበሩ፤” በማለት አሠራሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ለማስረዳት ሞክረዋል፡፡

  እንደ እሳቸው እምነት፣ ስልክ ደውሎ በተያዘ ቀጠሮ ሰዓት ጠብቆ የመገኘት አሠራር ያልተለመደ መሆኑ ምናልባት በጤና ተቋማቱ መጨናነቅ እንዲኖር አድርጓል፡፡ የሞራል ጥሰት የመሳሰሉ ነገሮችም በተቋማቱ ሠራተኞች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ ይህ ግን በሠራተኞቹ ሥነ ምግባር ጉድለት ሳይሆን በተገልጋዮቹ የሚነገራቸውን ነገር አለመቀበል ነው፡፡

  በጤና ተቋማቱ እንደ መጸዳጃ ቤት ያሉ አገልግሎቶችን ማግኘት ለሴቶቹ ቀላል አለመሆኑን፣ ሠራተኞች ሴቶቹን እንደሚያመናጭቋቸው፣ ይህ ሁኔታ ባሳደረባቸው ሥነ ልቦናዊ ተጽዕኖ ሴቶቹ ምርመራ በሚያደርጉባቸው ተቋማት ነፃ ሆነው መንቀሳቀስ ግልጽ ያልሆነላቸውን ነገርም ነፃ ሆነው መጠየቅ እስከ መፍራት መድረሳቸውን ለዶክተር ቴዎድሮስ ገለጽንላቸው፡፡

  “ሠራተኞች ተገልጋዮቹ ላይ እንደዚህ ዓይነት ነገር የሚያደርጉ ከሆነ ይህ በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት የለውም፡፡ የሥነ ልቦናውን ጫና ግን በተጓዦቹ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እስከ ኤርፖርት ድረስ አስተውያለሁ፡፡ ይፈራሉ፣ በዚህ ሒዱ ካልተባሉ አይንቀሳቀሱም፡፡ መብታቸውን ያለማወቅ ነገርም በተገልጋዮቹ በኩል አለ፡፡”

  ከወረፋ ጋር በተያያዘ ወደ ዓረብ አገሮች የሚሔዱ ሴቶች የምርመራ አገልግሎት ባሉ ተቋማት ችግር እንደሚገጥማቸው፣ ሠራተኞች ተገልጋዮች ጥያቄ ሲያነሡ እንደማያስረዷቸው፣ ሌሎችም ችግሮች እንደሚያጋጥማቸው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የውጭ ሥራ ስምሪት አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ መዝገቡ አሳፋ ናቸው፡፡

  እሳቸው እንዳሉት ሥራቸው ላይ ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖ ለማያሳድር የዓይን ችግር ተጓዥ ሴቶች የዓይን መነፅር ይታዘዝላቸዋል፡፡ እንዲገዙ የሚደረገውም ከተወሰኑ መነፅር ቤቶች ብቻ ነው፡፡ በሌላ በኩል ምርመራውን እየሰጡ ካሉ የሕክምና ተቋማት መካከል የላብራቶሪና ራጂ ምርመራ የሚሰጡባቸው ክፍሎች የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኙ አሉ፡፡

  ምርመራውን የሚሰጡ የጤና ተቋማት ውስን በመሆናቸው የሚፈጠር መጨናነቅን ተከትሎ የሚፈጠሩ ችግሮችን በማስመልከት ማኅበሩ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት አቤቱታውን በተለያየ ጊዜ ማቅረቡንም አቶ መዝገቡ ነግረውናል፡፡ ምናልባትም በቂ ማስረጃ ለጊዜው ባይኖርም ሴቶቹ በተቋማቱ አገልግሎት ላይ የሚያነሷቸው የተለያዩ ቅሬታዎች መኖራቸውንም ገልጸውልናል፡፡

  Read more »
 • In search of opposition parties worth their salt

  Ethiopia needs strong political parties which present the public with different alternatives on a range of issues. It would be difficult to build a stable democracy without strong and rival political parties.

  Of course, a true multi-party system does not necessarily equate with the proliferation of political parties of all stripes; it is actually about the existence of strong political parties which possess a strong political program, strong policies and strategies as well as a strong organization and leadership.

  As in any country, which has a multi-party system, Ethiopia has a ruling party, albeit one which has had overwhelming majority in parliament for over two decades now, and various opposition parties. It is no exception.

  However, in Ethiopia’s context there is a huge gulf between the ruling and opposition parties. On the one hand, the ruling Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF) asserts that it has an articulate political program, appropriate policies and strategies plus over five million members nationwide. On the contrary, the opposition camp is replete with political parties which, unlike the EPRDF, lack a clear political program, policies, strategies, organization and funding.

  Current global and local conditions are testing for all political parties operating in Ethiopia. The world is in the grip of an economic crisis and its impact has been and is being felt in Ethiopia. We expect the political parties active in the country to propose alternatives they deem to be solutions so that the public can demand that the alternative, which it feels is viable, be implemented. What we have been presented with to date, however, is the ruling party’s alternatives alone. We know nothing about how opposition parties plan to address the problem.

  The EPRDF is telling everyone that Ethiopia’s economy has shown a remarkable improvement under it. It claims the economy has grown at a double-digit rate for the past eight years, the highest in Africa, that it is poised to grow even faster thanks to the 5-year Growth and Transformation Plan (GTP) it is executing which, among others, involves raming up power production as well as mineral and industrial output, expansion of railway and road network, and ensuring food security. It points out that it has started to set up industrial zones in different parts of the country and that more are on the way, and that it is taking steps aimed at taming the rampant inflation, which has made life hard for the public. It also says that it has succeeded in attracting substantial Foreign Direct Investment from China, India and Turkey as well as in securing a significant volume of loans and grants from donors and lenders.

  How about opposition parties? What do you have to say for yourself? Please, present us with a choice of economic programs, policies and strategies which you believe is superior to the EPRDF’s and plan to implement if you were to take the reins of power.

  On the political front as well the EPRDF says it deserves kudos for delivering democracy, fundamental human and democratic rights like press freedom and freedom of assembly and thought, and free and fair elections to the people of Ethiopia.

  How do opposition parties acquit yourselves in this regard? Tell us what alternative programs, policies and strategies you are thinking of pursuing with respect to democracy, human rights, justice, elections, press freedom, etc if you were to be voted into office.

  Notwithstanding that it has been met with fierce criticism from some quarters, the EPRDF has made quite clear its position on Ethiopia’s foreign relations. Accordingly, it has said that Ethiopia reserves the right to conduct incursions into Somalia and Eritrea to counter the terrorist design of terror elements in Somalia and the sinister motives of the Eritrean regime, which is driven by consuming desire to destabilize Ethiopia, that it is committed to regional cooperation, and that will deepen ties with the likes of China while maintain friendly relations with the West.

  Opposition parties, please enlighten us what changes or improvements you will bring about in the country’s foreign relations should you unseat the EPRDF. Clarify your position, policies and strategies on Somalia, on Eritrea, on the IGAD and AU, on regional security, on Ethiopia’s ties with both the East and the West, etc.

  Let’s make one thing clear. We are not demanding opposition parties to abandon their political struggle. In fact we believe they should offer a stiff opposition to the EPRDF. Their struggle must be well-organized, broad-based and under pinned by viable and coherent programs, policies and strategies.

  We do not see opposition parties demonstrating such strength; we do not see them laying on the table an alternative set of programs, policies and strategies as well as enhancing their institutional strength.

  Needless to say the alternatives that opposition parties present the public with must neither be myopic nor tangential, they must rest on fundamental political, economic and social issues.

  Ethiopia lacks strong opposition parties at a time it needs them most, It’s crying out for them!

  Read more »
 • የትምህርት ፖሊሲው ምን እያፈራ ነው? ድንጋይ ጠራቢ ወይስ ባለሙያ?

  View Comments

  ባለፉት ጥቂት ዓመታት መንግሥት ለትምህርቱ ዘርፍ በመደበው ከፍተኛ በጀት የተቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ማስመረቃቸውን ተያይዘውታል፡፡

  በአገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል ማፍራት የሚችሉ ዩኒቨርሲቲዎች መገንባታቸው በበጐ ጐኑ የሚጠቀስ ተግባር ቢሆንም፣ በቂ ዝግጅት ባልተደረገበትና ሁለተኛ ዲግሪና ዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው መምህራን በበቂ ሁኔታ ባልተሟሉበት ሁኔታ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በለብ ለብ እንዲመረቁ መደረጉ በአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የሚፈጥረው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ በቀላሉ ሊታይ የማይችል መሆኑን፣ በዘርፉ ጥናት ያካሄዱ ምሁራን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

  በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተከፈቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስትምሩ አብዛኛዎቹ መምህራን የመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ያላቸው መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ከጐንደር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ዲፓርትመንቶች ለመመረቅ የተዘጋጁ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የመመረቂያ ጽሑፋቸውን በቡድን ተደራጅተው እንዲያቀርቡ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህ ክስተት የትምህርት ጥራት ምን ያህል እያሽቆለቆለ መሄዱን ያመለክታል፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ተማሪዎቹ በቡድን የመመረቂያ ጽሑፋቸውን እንዲያዘጋጁ የተደረጉት የመመረቂያ ጽሑፉን ሊገመግሙ የሚችሉ ብቃትና ክህሎት ያላቸው መምህራን ባለመኖራቸው መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡

  ‹‹ራሱ ስለመመረቂያ ጽሑፍ በቂ ዕውቀት ሳይኖረው የተመረቀ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር በተመሳሳይ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ተመራቂዎች ሊገመግም አይችልም፤›› ነበር ያሉት፡፡

  ከትምህርት ጋር በተያያዘ መንግሥት ከጥራት ይልቅ ብዛትን የመረጠበት መንገድ አሁንም ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነው፡፡ በዕውቀት የዳበረና ብቃት ያለው የተማረ ኃይልን ማፍራት የሚችሉ ብቁ መምህራንን አስቀድሞ ከማዘጋጀት ይልቅ በየክልሉ ሕንፃ ገንብቶ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በየዓመቱ እየተቀበለ፣ ከእነሱ ብዙም የተሻለ ዕውቀት በሌላቸው መምህራን አስተምሮ ማስመረቁ የአገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሥጋት ላይ የሚጥል መሆኑን ታዛቢዎች ሲገልጹ ነበር፡፡

  ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቁ ተማሪዎች ዕውቀቱና ችሎታው ቢኖራቸው እንኳን እነሱን ተቀብሎ ሊያስተናግድ የሚችል በቂ የሥራ ዕድል ሊገኝ ይችላል ወይ? የሚለውም የብዙዎች ጥያቄ ነበር፡፡ መንግሥት ሁልጊዜ የሚያቀርበው መከራከሪያ ተመራቂዎች ሥራ ፈጣሪ እንጂ ሥራ ፈላጊ መሆን የለባቸውም የሚል ነው፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ሕይወት በሚመራ ማኅበረሰብ ውስጥ ሥራ ፈጠራ የሚለው የመንግሥት መፈክር እውን ሊሆን አይችልም ሲሉ የመንግሥትን መከራከሪያ ያጣጥሉታል፡፡ አንድ ተመራቂ የሥራ ፈጣሪ ለመሆን በቂ መነሻ ካፒታል ሊኖረው እንደሚገባ በመጥቀስ፡፡

  ከዩኒቨርሲቲ ምሩቃንና ከሥራ አጥነት ጋር በተያያዘ በዘርፉ ባለሙያዎች ሲሰነዘር የቆየው ሥጋት በእርግጥም እውን የሆነ ይመስላል፡፡ አገሪቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር የምታወጣበት የትምህርቱ ዘርፍ የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ መሆን አልቻለም፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚወጡት በርካታ ምሩቃን ለሥራ አጥነት ተዳርገዋል፡፡ ሥራ ፍለጋ ሲባዝኑ ዓመታትን የሚያሳልፉ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መጥቷል፡፡

  እውን የሆነው ትንቢት
  ‹‹ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
  ተፈላጊ ባለሙያ፡- ግንበኛ
  ተፈላጊ ችሎታ፡- ከሕንፃ ኮሌጅ በድንጋይ ጠረባ ሁለተኛ ዲግሪ ያለውና በሙያው አምስት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሠራ/የሠራች፣ ወይም ከማንኛውም የግል ኮሌጅ ሦስተኛ ዲግሪ ያለውና በሙያው 25 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት
  ደመወዝ፡- 7 ሺሕ 7 መቶ ዘጠና
  አመልካቾች፡- የሥራና የትምህርት ማስረጃቸሁን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም አንድ የምትጠርቡትን ድንጋይ በመያዝ እስከ 13/2030 ድረስ ላፍቶ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
  ሴት ጠራቢዎች ይበረታታሉ፡፡
  ሌላ ማስታወቂያ
  ሙያ፡- ሐኪም
  ተፈላጊ ችሎታ፡- የታመሙ ሰዎችን አክሞ ማዳን የሚችል ከታወቁት የአገሪቱ 73 ዩኒቨርሲቲዎች በሕክምና ሙያ የተመረቀ/የተመረቀች በሙያው ቢያንስ 18 ዓመት የሠራ/የሠራች፡፡

  ማሳሰቢያ
  አመልካቾች የትምህርት የሥራ ማስረጃቸውን እንዲሁም አክመው ያዳኑትን 15 ሰዎች ለምስክርነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በእንስሳት ሐኪምነት የተመረቁ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  ሙያ፡- ፎርማን
  ተፈላጊ ችሎታ፡- በሲቪል ምህንድስና ወይም በአርክቴክቸር ወይም በተመሳሳይ ሙያ ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት እና በሙያው 35 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣
  ደመወዝ፡- 8 ሺ 8 መቶ ዘጠና
  አመልካቾች የትምህርት ማስረጃቸሁንና በታማኝነት ሊመሰክሩላችሁ የሚችሉ ሁለት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያስተማሯችሁን መምህራን ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ መምህራኖቻችሁ ስለናንተ ከመመስከራቸው በፊት በየሃይማኖታቸው ቃለ መሀላ ለመፈጸም ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
  ማሳሰቢያ፡-
  የትምህርት ማስረጃ ብቻውን ዋጋ አይኖረውም፡፡ እንግሊዝኛን በትክክል ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ተወዳዳሪዎች ሁለተኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ቢኖራቸውም እንኳ ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ ድርጅቱ ለማወዳደር የሚገደደው የመጀመሪያዎቹን 10 ሺ አመልካቾች ብቻ ይሆናል፡፡››

  ከላይ የተጠቀሰው የሥራ ማስታወቂያ ኢትዮጵያ በ2030 ዓ.ም. ምን እንደምትመስል ከሚተርከው የመሐመድ ሰልማን ትንቢታዊ ልብ ወለድ የተወሰደ ነው፡፡ የዛሬ 26 ዓመት የሚኖረውን የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን የሥራ ፍለጋ ሁኔታ የሚያስቃኘው የመሐመድ ሰልማን ትንቢት ተጽፎ አንድ ዓመት ሳይሞላው እውን የሆነ ይመስላል፡፡

  በተማሩበት የሙያ ዘርፍ በአገር ግንባታ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ከቶም አስበውትና አልመውት በማያውቁት ሥራ ውስጥ እንዲገቡ ተገድደዋል፡፡ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የመንግሥትን ሥራ ሳይጠብቁ በግላቸው ሥራ ፈጣሪዎች ሆነዋል ያላቸውን በአርዓያነት የሚጠቀሱ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን በማስመልከት ያቀረበው ዘገባ ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡ አንዳንዶቹ ያዩትን ማመን አቅቷቸዋል፡፡ ሌሎቹን ደግሞ ተስፋ አስቆርጧል፡፡

  መንግሥት ለፕሮፓጋንዳ ይጠቅመኛል ብሎ ባሰበው በዚህ ዝግጅት የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን አንድ ያልተማረ ዜጋ ሊሠራው በሚችለው የድንጋይ ጠረባ ሥራ ተሰማርተው ውጤታማ መሆናቸውን ገልጾልናል፡፡ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ሙያ የተመረቁ ወጣቶች በሚኖሩባት በአዲግራት ከተማ ድንጋይ ሲፈልጡ በዓይናችን በብርቱ አይተናል፡፡ ተመራቂዎቹም በድንጋይ ፈለጣ ሥራ ላይ ተሰማርተው የተሻለ ገቢ ማግኘታቸውን ገልጸውልናል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያሳየን ይህን ብቻ አይደለም፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በኮብል ስቶን ማንጠፍ ሥራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶችን በማስመልከት ጣቢያው ባሳለፍነው ሳምንት ባቀረበው ፕሮግራም ከዩኒቨርሲቲ በዲግሪ የተመረቀና ማስተርስ ዲግሪውን እየተከታተለ ያለ አንድ ግለሰብ በድንጋይ ጠረባ ተሰማርቶ ስኬታማ መሆኑን ገልጾልናል፡፡ ምሁሩ ድንጋይ ጠራቢም ይህንኑ አረጋግጦልናል፡፡ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንዲሉ የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያም ከአንድ ሳምንት በፊት ባስተላለፈው ፕሮግራም ከዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የተመረቀ ወጣት፣ ፊደል ያልቆጠሩ አባቶቻችን ከሦስት ሺሕ ዘመን በፊት ጀምሮ ሲጠቀሙበት የነበረውን የአስተራረስ ዘዴ ተረክቦ እሱም እንደ አባቱ በባዶ እግሩ በበሬ ሲያርስ አሳይቶናል፡፡ ይህንኑ ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ የሚከተሉት ወጣቱ ምሩቅና ጓደኞቹም በአርዓያነት ሊጠቀሱ የሚገባቸው ሥራ ፈጣሪዎች መሆናቸውን ጣቢያው ሊያስረዳ ሞክሯል፡፡

  ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና በአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ የተላለፉትን እነዚህን አስደንጋጭ ዘገባዎች የተመለከቱ ሰዎች ‹‹የመማር ጥቅሙ ምንድነው?›› ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ በዚህ ዘገባ የደነገጡትና በአገሪቱ ሁኔታ ተስፋ የቆረጡት የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ብቻ አይደሉም፡፡ ወላጆችና ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያከኮበኩቡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጭምር እንጂ፡፡

  ሰዎች ሕይወታቸውን ለመቀየር ከፈለጉ ምንም ዓይነት ሥራ መናቅ እንደሌለባቸው ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን ረጅም ዕድሜውን በትምህርት ያሳለፈ አንድ ባለሙያ በተማረበት የሙያ ዘርፍ በመሰማራት ፋንታ ወደታች ወርዶ ባልተማሩ ሰዎች ሊሠራ በሚችል የሥራ ዘርፍ ሲሰማራ ማየት ለማንም የሚዋጥ ተግባር አይደለም፡፡ መንግሥት በበጀተው በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ከየዩኒቨርሲቲው ትምህርት ተከታትለው የሚመረቁ ወጣቶች የመጨረሻ ዕጣ ፈንታቸው ኮብል ስቶን ማንጠፍ ከሆነ፣ ‹‹መማር ለምን ያስፈልጋል?›› የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡ ድሃ ቤተሰቦቹን አስቸግሮ ለዓመታት ትምህርቱን የተከታተለ ግለሰብ የመጨረሻ ሥራው ድንጋይ መጥረብ ከሆነ የመማር ጥቅሙ ምን ላይ ነው?

  ኃላፊነት የጐደለው ዘገባ?
  ሪፖርተር ያነጋገረው አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ግለሰብ፣ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ታናሽ ወንድሙ፣ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን በኮብል ስቶን ሥራ ላይ መሰማራታቸውን የሚገልጸውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከተመለከተ በኋላ፣ ‹‹ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ የሚጠብቀኝ ሥራ ድንጋይ መጥረብ ከሆነ ለምን እማራለሁ? ትምህርቴን አቋርጨ ልምጣ?›› የሚል ጥያቄ በማንሳት ሌት ተቀን ቤተሰቦቹን እየጨቀጨቀ መሆኑን ገልጿል፡፡

  ጉዳዩን በማስመልከት ለሪፖርተር አስተያየት የሰጡ አንድ ወላጅ በበኩላቸው፣ መንግሥት በቴሌቪዥን ያስተላለፈው ፕሮግራም ኃላፊነት የጐደለው መሆኑን ይናገራሉ፡፡

  አንድ ከዩኒቨርሲቲ የተመረቀ ወጣት የሚጐርሰውና የሚለብሰው ካጣ ሕይወቱን ለማቆየት ከትምህርት ደረጃው ጋር የማይመጣጠን ሥራ ለመሥራት ሊገደድ እንደሚችል፣ ይህም እንደ ትልቅ ውድቀት ሊቆጠር እንደማይገባ እኝሁ ግለሰብ ቢገልጹም፣ ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ወጣቶች በድንጋይ ጠረባ ሥራ መሰማራታቸውን የሚገልጸው ፕሮግራም በቴሌቪዥን መተላለፉ ግን ኅብረተሰቡ ለትምህርት የሚኖረውን አመለካከት የወረደ እንደሚያደርገው ይገልጻሉ፡፡

  ‹‹ሥራ አጥ ወጣቶቹ ኮብል ስቶን አንጣፊ ለመሆን መገደዳቸውን ስመለከት ሐዘን ቢሰማኝም ክስተቱ ከአገሪቱ ዕድገት ጋር የሚያያዝ በመሆኑ እምብዛም አላስደነገጠኝም፡፡ ፕሮግራሙ በቴሌቪዥን መተላለፉ ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንዲያመዝን ያደርጋል፡፡ ተምረን ጥሩ ደረጃ ላይ እንደርሳለን በማለት ነገን በተስፋ የሚጠብቁ ታዳጊ ወጣቶችን ተስፋ ያስቆርጣል፤›› በማለት ፕሮግራሙ በተማሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ያስረዳሉ፡፡ ችግሩ የትምህርት ፖሊሲ ነው?

  አንድ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ከዩኒቨርሲቲ ሲወጣ ተቀብሎ ሊያስተናግደው የሚችል ክፍት የሥራ ቦታ ይጠብቀዋል ተብሎ ቢታመንም፣ ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲተገበር አይታይም፡፡ የመንግሥትም ሆነ የግል ድርጅቶች አብዛኛውን ጊዜ የሥራ ልምድ ላለው ባለሙያ ዕድል መስጠታቸው አዲስ ተመራቂዎች የሥራ ዕድል እንዳይፈጠርላቸው አድርጓል፡፡ ልምድ ያለው ባለሙያ ሥራ እያማረጠ ከአንድ መሥርያ ቤት ወደሌላ መሥርያ ቤት በመዘዋወር ተጠቃሚ ሲሆን፣ አዲስ ተመራቂው ግን ሥራ ሲፈልግ ዓመታትን ያስቆጥራል፡፡ በዜሮ ዓመት የሥራ ልምድ መሥርያ ቤቶች ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ሲያወጡ ለአንድ የሥራ ቦታ የሚያመለክቱ ምሩቃን በመቶዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ቀጣሪ መሥርያ ቤቶች ይገልጻሉ፡፡ አመልካቾቹ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ለፈተና ወይም ለቃለ ምልልስ ሳይጠሩ የሚቀሩት ሥራ ፈላጊዎች በጣም ብዙዎች ናቸው፡፡

  ቀደም ባሉት ጊዜያት አንድ ከዩኒቨርሲቲ የተመረቀ ወጣት በቀላሉ ሥራ ያገኛል ተብሎ ይታመን ነበር፡፡ ‹‹ልጃችን ከዩኒቨርሲቲ ሲመረቅ ሕይወታችን ይስተካከላል›› በሚል እምነት ነገን በተስፋ የሚጠባበቁ ወላጆች ነበሩ፡፡ አሁን አሁን ግን ነገሩ ተቀይሯል፡፡ ‹‹ልጄ ሥራ ይዞ ይረዳኛል›› የሚለው የወላጆች ተስፋ ‹‹ልጄ ለምን ያህል ጊዜ ሥራ ፈት ሆኖ ይቆይ ይሆን?›› ወደሚል ጭንቀት ተቀይሯል፡፡

  መንግሥት በርካታ ዩኒቨርሲቲዎችን ከማቋቋሙ በፊት ዩኒቨርሲቲ የመግባት ዕድል ማግኘት በጣም ከባድ ነገር ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ከባዱ ነገር ዩኒቨርሲቲ መግባት ሳይሆን ሥራ ፈልጐ ማግኘት መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡

  አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ችግሩን መንግሥት ከሚከተለው የትምህርት ፖሊሲ ጋር ያገናኙታል፡፡ በየዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡት የትምህርት ዓይነቶችም ተማሪዎችን ለሥራ የሚያዘጋጁ አለመሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሆነው የሠሩትና የዌልስ ኢንስቲትዩት ዩኒቨርሲቲ የኤዱኬሽን ፕሮፌሰር የሆኑት ኬት አሽክሮፍት ባለፈው ዓመት ባወጡት ጥናት፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በፍጥነት እያስፋፋች ቢሆንም የትምህርት ጥራት መጓደል፣ ሙያዊ ዕውቀት ያለው አመራር እጥረት፣ ተቋማዊ መዋቅርና ተልዕኮ የአገሪቱ ተግዳሮቶች ሆነው መቀጠላቸውን አመልክተዋል፡፡

  ከአሥር ዓመት በፊት በአገሪቱ የነበሩት ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ወደ 22 ማደጋቸውንና ሌሎች አሥር ዩኒቨርሲቲዎች በቅርቡ የሚከፈቱ መሆኑን የጠቆመው ይኼው ጥናት፣ ዩኒቨርሲቱዎች ቢስፋፋም ጥራት ያላቸውን ምሩቃንን በማፍራት ረገድ ችግር የተፈጠረ መሆኑን ይገልጻል፡፡

  ‹‹የትምህርት ጥራትን ለመቆጣጠር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ የተቋቋመ ቢሆንም፣ በቀጣሪው ድርጅት ፍላጐትና በተቋማቱ ካሪኩለም፣ ፔዳጐጂና የምዘና ዘዴዎች መካከል አለመጣጣም አለ፡፡ ለተለያዩ ጥናቶች ያነጋገርኳቸው ቀጣሪዎችና ሌሎች አካላት በራስ የሚተማመን፣ ተነሳሽነት ያለው ጠያቂና ፈጣሪ ምሩቅ እንደሚፈልጉ ገልጸውልኛል፤›› የሚሉት አጥኝዋ፣ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ግን ይህንን የቀጣሪዎችን ፍላጐት ማሟላት አለመቻላቸውን ይገልጻሉ፡፡

  እርሳቸው እንደሚሉት የትምህርት ተቋማት በተስፋፉ ቁጥር ሙያዊ ብቃት ያላቸው ሠራተኞች አስፈላጊነት እየጨመረ መምጣቱ የማይቀር ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ግን ይህን ማሟላት አልቻለችም፡፡ ‹‹አብዛኛዎቹ የተቋማቱ አስተዳደር አባላት ከብዙ ተማሪዎች ጋር ተስማምቶ የሚሄድ ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችል ውስን አቅም ነው ያላቸው፤›› ይላሉ፡፡

  በሌሎች አገሮች መንግሥታት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሲያስፋፉ የሚከፍቷቸው ተቋማት የተለያዩ ተልዕኮዎች እንዲኖራቸው በማድረግ (ለምሳሌ ስፔሻሊት ኮሌጅስ፣ ጁኒየር ኮሌጅስ፣ አፊሌትድ ኮሌጅስ፣ ፖሊ ቴክኒክስ፣ ፖስት ግራጁየት ኢንስቲትዩሽንስ፣ ወዘተ) እያሉ በሚገነቧቸው ኮሌጆች የተለያየ ሙያና ብቃት ያላቸውን ምሩቃን እንደሚያፈሩ የሚገልጹት ፕሮፌሰር አሽክሮፍት፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ከብዝኀነት ይልቅ አንድ ዓይነት የትምህርት ሥርዓት ለመዘርጋት ወስኗል፤›› በማለት ኢትዮጵያ የገጠማትን ተግዳሮት ያስረዳሉ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለዕድገት ወሳኝ መሆናቸውን መንግሥት ቢያምንም፣ ዕድገትን በማምጣት ረገድ የተቋማቱ ሚና ምን መሆን አለበት? ወይም ምን መሥራት አለባቸው? በሚለው ጉዳይ ላይ ወጥ የሆነ አቋም የለውም፡፡ ለዚህ ድምዳሜያቸው ዓይነተኛ ምሳሌ ነው ብለው ያቀረቡትም መንግሥት መጀመሪያ ላይ ማኅበራዊ ሳይንስን በሚመለከት ሲያራምደው የነበረውን አቋም ነው፡፡

  አዲስ የተቋቋሙት ዩኒቨርሲቲዎች በማኅበራዊ ሳይንስ ላይ ማተኮር እንዳለባቸው ሌሎች አዳዲስ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ፋኩልቲዎች ደግሞ ቀስ በቀስ እንደሚከፈቱ መንግሥት ዕቅድ ይዞ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን የሚያስታውሱት ፕሮፌሰሯ፣ ብዙም ሳይቆይ ግን ፖሊሲውን በመቀየር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ካሪኩለማቸውን ቀይረው 70 በመቶ የሚሆኑትን ተማሪዎቻቸውን ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲያጠኑ ይደረግ የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉን ይገልጻሉ፡፡ አያይዘውም ‹‹ላብራቶሪዎችና ወርክሾፖች ከመቋቋማቸውና ተማሪዎችን የሚያስተምሩ መምህራን ከመሠልጠናቸው በፊት አዲሶቹ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት እንዲቀየሩ ተደርጓል፤›› ይላሉ፡፡

  እንደ ፕሮፌሰር አሽክሮፍት ሁሉ ሌሎች አጥኝዎችም የኢትዮጵያ መንግሥት እየተገበረው ያለው የትምህርት ፖሊሲ ለትምህርት ጥራት መውደቅና ለሥራ አጥነት ምክንያት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ መንግሥት ግን ስህተቱን የተገነዘበ አይመስልም፡፡ በየዓመቱ ከየዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁ ወጣቶች ሥሪ ፈጣሪ እንጂ ሥራ ፈላጊ መሆን የለባቸውም የሚለውን እምነት ይዞ አሁንም እየተጓዘ ያለው መንግሥት፣ ‹‹ለዩኒቨርሲቲ ምሩቃን የሥራ አጥነት ችግር ዋነኛው መፍትሔ ‹‹ድንጋይ ጠራቢነት ነው›› የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰ ይመስላል፡፡ በሚቀጥሉት ዓመታት ስንት ድንጋይ ጠራቢ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ይኖሩን ይሆን?

  Ethiopian Reporter

  Read more »
RSS