Amharic Tube - All Amharic TV Channels and Shows
Welcome
Login

በዓይነቱ ልዩ የሆነው ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ Washington Medical Center built by Ethiopian diaspora returnees and local doctors inaugurated in Addis Abeba

[ሰንደቅ ጋዜጣ]

በአሜሪካ ከ25 ዓመታት በላይ በህክምና ሙያ ሲያገለግሉ በቆዩ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሀኪሞች እና በሀገር ውስጥ ባሉ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሀኪሞች ጥምረት የተቋቋመው ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር ዘመናዊ በሚባሉ የህክምና መስጫ መሳሪያዎችና ባለሙያዎች ተደራጅቶ ባለፈው ቅዳሜ ተመርቆ ዕለት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ቦሌ ሩዋንዳ ኤምባሲ ፊት ለፊት የሚገኘው ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተርን መርቀው የከፈቱት የኢፌዲሪ ንግድ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሊ ሲራጅ ናቸው። አቶ አሊ በወቅቱ እንደተናገሩት ባለፉት አስር ዓመታት ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ ባለችው ኢትዮጵያ ከኢኮኖሚው ጋር የሚጓዙና ደረጃቸውን የጠበቁ የህክምና ተቋማትን ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ ሀገራቸውን ለማገልገል ወደ ሀገር በቤት በተመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተከፈተው ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል። የዚህ አይነት ተቋማትንም መንግስት ከጎናቸው ሆኖ እንደሚያግዝም ተናግረዋል።

የዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር የረጅም ዓመታት ሙያዊ እውቀታቸውና ልምዳቸውን ይዘው ወደ ሀገር ቤት በተመለሱ ኢትዮ-አሜሪካውያንና በሀገር ውስጥ በሚሰሩ ባለሙያዎች በ60 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር ካርድ ከማውጣት ጀምሮ በዘመናዊ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የሚከናወን እንደሆነ ጠቅሰው የታካሚዎች የህክምና ሪከርድም ከወረቀት ነፃ ሆኖ በኮምፒውተር የሚገናኝ እንደሆነና ማዕከሉን የራሱ መድኃኒት ቤት ዘመናዊ አምቡላንስ፤ ዲጂታል የኤክስ ሬይ ማሽን፤ አልትራ ሳውንድ፣ ኢ ኬ ጂ ምርመራ እና ዘመናዊ ላቦራቶሪ የተደራጀ መሆኑን አስረድተዋል። ማዕከሉ በቀጣይነትም ሙሉ በሙሉ ወደ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማሳደግ ተደራሽነቱን እና አገልግሎቱን እንደሚያሰፋ ዶ/ር ማርቆስ ጨምረው አስታውቀዋል።

ሀገርንና ወገንን የማገልገል ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ወደ ሀገር ቤት በተመለሱ ስፔሻሊስት ሀኪሞች የተቋቋመው ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር አገልግሎቱን ለሁሉም ታካሚ ተደራሽ ሊባል በሚችል ተመጣጣኝ ዋጋ ለሀገር ውስጥና ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ ዲፕሎማቶችና የውጭ ሀገር ሰዎች በአካል፤ በስልክ፤ በኢንተርኔት በሚያዝ ቀጠሮ የማዕከሉን ስፔሻሊስት ዶክተሮች ማግኘት እንደሚቻል የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ፋሲል ተፈራ ገልፀዋል።

‘ለሁሉም የውስጥ ደዌ ህመሞች በሙያው የካበተ ልምድ ያላቸውን ሀኪሞች ለ24 ሰዓታት የህክምና አገልግሎት ይሰጣል። አስፈላጊ ሲሆንም የተለየ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ሌሎች ስፔሻላይዝድ የሆኑ ሀኪሞችን በሀገር ውስጥ ባሉና ከውጪ ሀገር በማስመጣት ተጨማሪ የሙያና የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት ሥርዓትም ተዘርግቷል’ ብለዋል ዶ/ር ፋሲል።

ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር ተመርቆ ስራውን ሲጀምር ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ የህክምና ባለሙያዎች፤ ዲፕሎማቶች አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በአሜሪካ የተማሩና ያገለገሉ ሀኪሞች ይህንን ሜዲካል ሴንተር ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ለመክፈት የአንድ ዓመት ጊዜ የወሰደባቸው ሲሆን ለማዕከሉ እውን መሆን መንግስት አስፈላጊ የሆኑ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ከማድረግ ጀምሮ የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ሙሉ ድጋፍ ማድረጋቸው ተዘግቧል።

Receive Ethiopian News and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።

 

Post your comment

Comments

Be the first to comment
Watch new Ethiopian movies. Visit the new Sodere.com website or download the mobile application for iPhone and Android. Choose your phone type. iPhone   Android     iPad

Related Articles

 • Arfaj full Ethiopian movie
  Arfaj full Ethiopian movie

  Download Sodere app and watch Arfaj full movie የሶደሬ አፕልኬሽንን በማውረድ አርፋጅ ሙሉ ፊልም ፊልም በነፃ ተመልከቱ Choose your platformiPhone And...

 • Enafatalen full Ethiopian movie
  Enafatalen full Ethiopian movie

  To pay with PayPal or direct credit card በፔይፓል ወይም በቀጥታ ካርድ ለመክፈል click buy now button and click proceed to check out. Ent...

 • ትዝም Tizim full Ethiopian movie
  ትዝም Tizim full Ethiopian movie

  To pay with PayPal or direct credit card በፔይፓል ወይም በቀጥታ ካርድ ለመክፈል click buy now button and click proceed to check out. Ent...

RSS